Quran.et Logo
am

surah113

አል-ፈልቅ የጎህ መቅደድ ምዕራፍ
ድምፅ አቅራቢ (Qari)
የአጫዋች ሁነታ (Play Mode)
1
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ

قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ

በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡

2

مِن شَرِّ مَا خَلَقَ

«ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፡፡

3

وَمِن شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ

«ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ፤

4

وَمِن شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ

«በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፡፡

5

وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ

«ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ፤ (እጠበቃለሁ በል)፡፡»